የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ሆነው ተመረጡ

By Mikias Ayele

September 19, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የቱሪዝም ሻምፒዮን ሆነው ተመረጡ።

የኢጋድ ፅህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ÷ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲሱ የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን መሆናውን ስንገልፅ ኩራት ይሰማናል ብሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለራዕይ መሪነት በቀጠናው ቱሪዝምን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር በኢጋድ አባል ሀገራት ዘንድ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት፣ ቅርሶችን እና አካባቢን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አስገንዝቧል፡፡