ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቴንስ የሚያደርገውን ሣምንታዊ በረራ ከፍ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

September 18, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ በሣምንት ሥድስት ቀን ለመብረር የሚስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ሣምንታዊ የበረራ ቁጥሩን ከፍ ከማድረጉ በፊት ወደ አቴንስ የሚያደርገው ሣምንታዊ በረራ አራት ጊዜ እንደነበርም ነው አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀው፡፡