Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሮማ አሰልጣኝ ዳንዔል ዲ ሮሲን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያኑ ክለብ ሮማ አሰልጣኝ ዳንዔል ዲ ሮሲን ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

አሰልጣኙ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሮማን ስኬታማ ማድረግ አልቻሉም በሚል ነው፡፡

ከአደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሦስቱን በአቻ አንዱን በሽንፈት ማጠናቀቃቸውም ዲ ሮሲ እንዲሰናበቱ አድርጓል ተብሏል፡፡

እስከ አሁን ያለውን ውጤት ተከትሎም ሮማ በጣሊያን ሴሪዓ 16ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዲ ሮሲ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪኒሆን ተክተው ለሰባት ወራት ሮማን በዋና አሰልጣኝነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡

Exit mobile version