Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ዛሬ ሲቀጥል ማንቼስተር ሲቲን ከኢንተርሚላን የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ላይ የጣሊያኑ ቦሎኛ ከዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ እንዲሁም የቼክ ሪፐብሊኩ ክለብ ስፓርታ ፕራግ ከኦስትሪያው ሬድቡል ሳልዝበርግ ይገናኛሉ፡፡

በሌላ በኩል የስኮትላንዱ ሴልቲክ ከስሎቫኪያው ስሎቫክ ብራቲስላቫ፣ ክለብ ብሩጅ ከቦሩሺያ ዶርቱመንድ፣ ማንቼስተር ሲቲ ከኢንተርሚላን፣ ፒኤስጂ ከስፔኑ ዢሮና በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

ትናንት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ጁቬንቱስ ፒኤስቪ አይንድሆቨንን 3 ለ 1፣ አስቶንቪላ የስዊዘርላንዱን ያንግ ቦይስ 3 ለ 0፣ ባየርንሙኒክ የክሮሺያውን ዳይና ሞዛግሬብ 9 ለ 2፣ ሪያልማድሪድ ስቱትጋርትን 3 ለ 1፣ ሊቨርፑል ኤሲሚላንን 3 ለ 1፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሊልን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

Exit mobile version