የሀገር ውስጥ ዜና

በየነ ጴጥሮሥ(ፕ/ር) የፅናት ተምሣሌትነታቸው ሁልጊዜም ሲዘከር የሚኖር ነው – ምክር ቤቱ

By Meseret Awoke

September 17, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በየነ ጴጥሮሥ (ፕ/ር) የፅናት ተምሣሌትነታቸው ሁሌም ሲዘከር የሚኖር እንደሆነ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ውሥጥ ጉልህ ድርሻ በነበራቸው በየነ ጴጥሮሥ(ፕ/ር) ህልፈት ሀዘኑ መሪር መሆኑን ምክር ቤቱ ከፋና ብሮድካሥቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።

የምክር ቤቱ ሠብሣቢ አቶ ደሥታ ዲንቃ ፥ በተለያዩ ዘርፎች የምክርቤቱን አቅም ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።

በፅናት ሠላማዊ የትግል ምርጫን ያሥቀደሙ እንደነበሩ አንስተው ፥ በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ላይም የማያወላውል አቋም እንደነበራቸው ነው ያስታወሱት።

ምክርቤቱ በእሳቸው ህልፈት የተሠማው ሀዘን ጥልቅ መሆኑን ገልጸው ፥ ለቤተሠቦቻቸው እና ዘመድ ወዳጆቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል ።

በሰለሞን ይታየው