አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ጎፈሬ የትጥቅ አምራች ኩባንያ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የዳኞች ትጥቅ አቅርቦት የአጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።
በፊርማ ሥነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የጎፈሬ መስራችና ባለቤት አቶ ሳሙኤል መኮንን እንዲሁም የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባበል ተገኝተዋል።
ለሦስት ዓመታት በሚቆየው ስምምነት ጎፈሬ ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዳኞች አራት ዓይነት ትጥቆችን ጨምሮ የማሟሟቂያ ፣ የጉዞ እና ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ የሚጠቀሙባቸው ቲሸርቶች እንዲሁም ቱታ በስፖንሰር መልክ ያቀርባል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር በሚካሄዱ ሌሎች ውድድሮች እንደ የደረጃቸው ቅናሽ የተደርገባቸው ትጥቆች በኩባንያው እንደሚቀርቡ መገለፁን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡