Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሜታ የሩሲያ መንግስት የዜና ምንጭ የሆነውን አር ቲ ማገዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንስታግራም እና ፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያዎች ባለቤት የሆነው ሜታ ኩባንያ የሩሲያ መንግስት የፖሊሲ እና የመረጃ ምንጭ የሆነው አር ቲ የዜና ወኪል ከገፁ ላይ ማገዱን አስታወቀ፡፡

ውሳኔው ዋሽንግተን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን በስለላ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ስትል መክሰሷን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን የገለጸው ሜታ ኩባንያ÷ ውሳኔው በሚቀጥሉት ቀናት ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ጠቁሟል።

የአሜሪካ መንግስት ባለፈው ሳምንት በአር ቲ ላይ ማዕቀብ መጣሉን መግለጹ ይታወቃል።

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም አርቲ የሩሲያ የስለላ ድርጅት ሆኖ እየሰራ ነው ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሞስኮ በበኩሏ ማዕቀቡን የኢንፎርሜሽን ጦርነት ነው ስትል የገለፀች ሲሆን፤ አሜሪካ ፍትሃዊ መረጃን በማቅረብ ረገድ ከሩሲያ ጋር መወዳደር አለመቻሏን የሚያሳይ ነው ብላለች፡፡

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሜታ ኩባንያ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን እንዲታገድ ጥያቄ ላቀረቡ የአውሮፓ ሀገራት ትብብር ሲያደርግ ቆይቷል መባሉን አር ቲ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version