Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢራን ፕሬዚዳንት ወደ አሜሪካ ሊያመሩ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

ፕሬዚዳንቱ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ለመታደም በመጪው እሁድ በአሜሪካ ኒውዮርክ እንደሚገኙ ተሰምቷል፡፡

በጉባኤው ተገኝተውም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢራናውያን ጋር የሚደረግ ውይይትን ጨምሮ በርካታ ስብሰባዎችን እንደሚያደርጉም ተነግሯል።

በተመሳሳይ መሪው ከተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኑር ኒውስ ነው።

Exit mobile version