ስፓርት

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነ

By Mikias Ayele

September 16, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

በታንዛንያ አስተናጋጅነት በሚካሄው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ሹመት ተከናውኗል።

በዚህ መሠረትም በዋና አሰልጣኝነት ስዩም ከበደ ፤ በረዳት አሰልጣኝነት ደግሞ ዐቢይ ካሣሁን እና አምሳሉ እስመለዓለም ሆነው ተሾመዋል።

ለውድድሩ ዝግጅት የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር ዛሬ ይፋ እንደሚደረግና ከነገ ጀምሮ በመሰባሰብ ዝግጅት እንደሚጀምሩም የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡