ስፓርት

ኢትዮጵያ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔን እንድታስተናግድ ተወሰነ

By Mikias Ayele

September 16, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡

ጉባዔው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንዲካሄድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም÷ ሀገሪቱ ማስተናገድ እንደማትችል ማሳወቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጉባዔውን ለማካሄድ ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በጥቅምት ወር በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ መገለጹን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡