የሀገር ውስጥ ዜና

በተለያዩ ክልሎች የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

September 16, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ በተለያዩ ክልሎች ተጀምሯል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢሳያስ እንድሪያስ እንዳሉት÷ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት ተደርጎ ወደተግባር ተገብቷል፡፡

የተማሪ ውጤት ለማሻሻል በተቀናጀ መንገድ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ክትትል እንደሚደረግ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የ2017 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ መጀመሩን የክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በአሰፈሩት ጽሑፍ÷ የዘንድሮው የመማር ማስተማር ሥራ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል ብለዋል፡፡