የሀገር ውስጥ ዜና

የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው

By Shambel Mihret

September 15, 2024

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ የሐይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሐይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው።

በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ያለውን በዓል የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጣኻ ሀሩን ቁርአን በመቅራትና ዱዓ በማድረግ በይፋ የሚያስጀምሩት ይሆናል።

በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰደቃ፣ በመንዙማና በነሺዳ በሀይማኖት አባቶች በወጣቶች እና በታዳጊዎች መርሐ ግብር እንደሚከበር ኢዜአ ዘግቧል፡፡