የሀገር ውስጥ ዜና

የመውሊድ በዓል እየተከበረ ነው

By Shambel Mihret

September 15, 2024

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

የመውሊድ በዓል የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) መልካም ተግባራትን የህይወት መርሕ ለማድረግ በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።

በዓሉ በኢትዮጵያ “የሰላሙ ነብይ” በሚል መሪ ቃል የነብዩ መሀመድ (ሰዐወ) በረከቶች በማስተዋል መንገዳቸውን በማሰብ እየተከበረ ይገኛል።