የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 34 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

September 14, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 34 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ 1 ሺህ 22 ወንዶች፣ 10 ሴቶችና 2 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ÷ከእነዚህ መካከልም 26 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡