Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በወቅቱ ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን በወቅቱ ተቀብለው ለማስተማር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ÷ በ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትንና አጠቃላይ አፈፃፀም ለመከታተል የሚያስችል ስምምነት ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እንደሚፈራረምም አንስተዋል፡፡

ስምምነቱ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባለፈ ሥራዎችን ቆጥሮ በመስጠት አፈፃፀማቸውን ለመከታተል የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በእውቀትና ክሕሎት የበቁ ተማሪዎችን በማፍራት ለሀገርና ሕዝብ የላቀ አበርክቶ እንዲኖራቸው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ይገኛሉ ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version