Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ በ2017 ከ10 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የትምህርት ዘመን 10 ነጥብ 1 ሚሊየን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ገለጹ፡፡

የተማሪዎች የምገባ መርሐ-ግብር የትምህርት ተሳትፎና የውጤታማነት ችግሮች መፍቻ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው÷  ይህን ታሳቢ በማድረግ በተጠናከረ መልኩ እየተተገበረ ነው ብለዋል፡፡

በዘንድሮው ትምህርት ዘመንም በ20 ሺህ ትምህርት ቤቶች 10 ነጥብ 1 ሚሊየን የቅድመ መደበኛና 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር አገልግሎት የማይውሉ ቦታዎችን በተቀናጀ ግብርና የማልማት ስራ እንደሚከናወንም አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version