የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል ነገ እሁድ ይከበራል

By ዮሐንስ ደርበው

September 14, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል ነገ እሁድ እንደሚከበር የመውሊድ በዓል አከባበር ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ ሼክ አብድልሀሚድ አሕመድ በሰጡት መግለጫ÷ በዓሉ “የሰላሙ ነብይ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡

በዓሉ ሲከበር የነብዩ መሀመድን በረከቶች በማስተዋል መንገዳቸውን በማሰብ መሆን እዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አቅም የሌላቸውን በመጎብኘትና ካለው በማካፈል እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ