ስፓርት

በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው ገቡ

By Melaku Gedif

September 13, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም ብራሰልስ በተካሄደ የ2024 ዳያመንድ ሊግ 5 ሺህ ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገቡ።

በውድድሩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:43.66 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ቀዳሚ ሆኗል።

አትሌት በሪሁ አረጋዊን በመከተል ሀጎስ ገብረህይወት 12:44.25 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ጥላሁን በቀለ 12:45.63 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃ ይዘው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።