አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፤ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
አምባሳደር ታዬ፤ በሶማሊያ ከድህረ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) በሚኖረው የኃይል ስምሪት ዙሪያ ኢትዮጵያ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ ያለቻቸውን ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው አንስተዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በቀጣናው ያለውን ውጥረት የማረገብ ሥራ እያከናወነች መሆኑንም ገልፀዋል።
መንግሥት ለፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት ሙሉ ተፈጻሚነት ያለውን ቁርጠኝነትም በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
አምባሳደር ታዬ አሜሪካ የኢትዮጵያን የአጋዋ ጠቃሚነት እገዳ በማንሳት ወደ ቀድሞው ትግበራ እንድትመልስ ጥሪ አቅርበዋል።