የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከተመድ ዋና ፀሃፊ ልዩ መልዕከተኛ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

September 13, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሃፊ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕከተኛ  ሃና ቴቴህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ እና የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ መክረዋል።

በዚህ ወቅት አምባሳደር ታዬ÷ ተመድ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንደ ምስራቅ አፍሪካ ዋና ተወናይ ሀገርነቷ ከሌሎች ሀገራት ጋር በመተባባር በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን የዲፕሎማሲ ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡