አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት የሙሉ አባልነት ሰርተፊኬት ተቀብላለች፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት የኢትዮጵያን 88ኛ የሙሉ አባልነት የማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት አባል መሆኗ በርካታ ፋይዳዎች እንዳሉት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከተለያዩ ሀገራት ጋር የኢንዱስትሪ ትስስር ለመፍጠር እና በክህሎት ልማት ከተቀረው የዓለም ክፍል ልምድ መለዋወጥ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል፡፡
በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልምዶችን በመቅሰም በዘርፉ እየተሠራ ባለው ሥራ የተሻለ ለውጥ ለማምጣትና ከተቀረው የዓለም የክህሎት ልቀት ጋር እኩል ለመራመድ ሰፊ ምህዳር እንደሚፈጥርም አስረድተዋል፡፡