የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

By ዮሐንስ ደርበው

September 12, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተቋሞቻቸው በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አገልግሎቶችን ከማዘመን፣ ከእጅ ንክኪ ነፃ አገልግሎት ከመስጠት፣ የውስጥ አሠራር ሥርዓቶችን ከማዘመን እና ቀልጣፋ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ከመዘርጋት አንፃር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት መደረሱን ወይዘሮ ሰላማዊት ተናግረዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ከማድረግ አኳያ ኢትዮ ቴሌኮም ተቋማቸው የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ መሆኑን የገለጹት ፍሬህይወት ታምሩ፤ አሁን የተደረሰው የትብብር ስምምነትም የዲጂታላይዜሽን አተገባበርን ለማላቅ ትልቅ ዕድል እንደሚሰጥ መናገራቸውን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡