አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኢንዱስትሪው በተያዘው የበጀት ዓመት 250 የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ ለማምረት አቅዶ እየሠራ መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡
ከዚህ ዕቅድ ውስጥ በመጀመሪያ ዙር 39 የ “N7 ፒክ አፕ” ገጣጥሞ ለደንበኞቹ ለማቅረብ የምርት ግብዓት ማስገባቱን ከግሩፑ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
አዲሱ የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ የዘመኑ የመጨረሻ ምርት እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ያሟላ መሆኑም ተገልጿል፡፡