የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

By amele Demisew

September 11, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ዓመታዊው የአዲስ ዓመት ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት በቤተ መንግሥት ተካሂዷል።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል።