አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 ዓ.ም ሀገራዊና ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ(ኢ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ የ2017 ዓ/ም አዲስ አመትን አስመልክቶ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተቋሙ ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት ህግና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማስከበር እና የሰራዊቱን አቅም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡
የተቋሙን አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነትና ትብብር ማሳደግና የሚዲያና የኮሙኑኬሽን ስራም በትኩረት እንደሚከወን ሚኒስትሯ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡