Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ዓመትን አስመልክቶ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ በአዲስ አበባ ሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል በመገኘት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።

ፕሬዚዳንቷ በወቅቱ÷ አዲስ ዘመን በግድ ተስፋ እንድናደርግ የሚጋብዘን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አዲስ ዓመትን በመረዳዳትና በመተሳሰብ ማሳለፍ እንደሚገባ ገልጸው÷ ዛሬ የተደረገው ማዕድ ማጋራት ብቻ ሳይሆን ታዳጊ ሴቶችን ለማበረታታትና ከጎናቸው መሆናችንን ለማሳየት ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ያደኔ ብርሃኑ በበኩላቸው÷ ፕሬዚዳንቷ ያደረጉት የማዕድ ማጋራት ሕጻናቱን የሚደግፍና ይበልጥ ተስፋ እንዲሰንቁ ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ለተደረገው የማዕድ ማጋራትም ምስጋና ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

Exit mobile version