አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን ሕዝባችንን የምንክስበትና ዝቅ ብለን የምናገለግልበት የመሻገር ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም÷ በሕዝባችን ሰላም ፈላጊነት፣ በአመራራችን ቁርጠኝነት ባሳለፍነው ዓመት የገጠሙንን ዓይነተ- ብዙ እና ተለዋዋጭ ፈተናዎች በጽናትና በትዕግስት አልፈናል ብለዋል፡፡
አሁን ሕዝባችንን የምንክስበትና ዝቅ ብለን የምናገለግልበት የመሻገር ምዕራፍ ላይ ደርሰናልም ነው ያሉት፡፡
በአዲሱ ዓመት ሁላችንም በአንድነት እና በኅብረት በመቆም ለመጭው ትውልድ መልካም ነገር በመስራት ከእዳ ወደ ምንዳ የምንሸጋገርበት የስኬት እና የብልጽግና ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡