Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ፎረሙ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

ወ/ሮ ጫልቱ በዚህ ወቅት÷ የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለስኬት እንዲበቃ ማድረጋችን ኢትዮጵያ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ለማዘጋጀት ያላትን አቅም ያሳያል ብለዋል፡፡

መድረኩ ብዙ የተማርንበትና ያለንን እምቅ አቅምና ተሞክሮ ለአፍሪካ ወንድሞቻችን ያካፈልንበትና እኛም የተማርንበት ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሀገራዊ ዕውነታችንን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሳየንበት በመሆኑ ይህ ዕድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ተስፋን ይዞ የመጣ የቀጣይ ዘመን ስጦታችን ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ ፎረሙ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉም አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version