Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ468 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ468 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርገዋል፡፡

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 463ቱ በሙሉ ይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከእነዚህ መካከልም 453ቱ ወንዶችሲሆኑ÷ 10ሩ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል አራት ወንድ እና አንድ ሴት ታራሚዎች የእስር ጊዜያቸው እንዲቀነስላቸው ውሳኔ መተላለፉ ተጠቁሟል፡፡

አቶ እንዳሻው የይቅርታ ተጠቃሚዎች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ በመልካም ሥነ-ምግባራቸው ምሳሌ በመሆን ህብረሰተሰቡን እንዲክሱ አሳስበዋል።

Exit mobile version