አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በትራንስፖርት ተርሚናሎች ተገኝተው ለአሽከርካሪዎችና ተጓዦች “እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ” የመልካም በዓል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሚኒስትሩ በላምበረትና አዲስ ከተማ (አውቶቢስ ተራ) የህዝብ ትራንስፖርት ተርሚናሎች ከማለዳው 10 ሰዓት በመገኘት ነው የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።
በማለዳው በበዓል ዋዜማ በስራ ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችና በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማክበር የሚሄዱ መንገደኞች ሚኒስትሩ የበዓል የአበባየሆሽ ዝማሬ ከሚያቀርቡ ታዳጊዎች ጋር በመሆን ነው በተርሚናሎቹ የተገኙት።
በዓልን በስራ ላይ እያሳለፉ ያሉት አሽከርካሪዎች የመልካም በዓል ካርድ ስጦታ መበርከቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡