Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ከጅቡቲ የንግድና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ከጅቡቲ የንግድና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዌዲ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትር ጉዌዲ የባቡር መስመሩን ከስትራቴጂካዊ ወደቦች ጋር በማስተሳሰር ቀጣናዊ ንግድን ለማሳለጥ እያደረጉት ላለው ያላሰለሰ ጥረትና አመራር ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ይህም የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ እድገት የሚጨምርና ትብብራቸውን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አገልግሎት የኃይል መቆራረጥ እንዳያጋጥመው ላደረጉት ድጋፍም አመስግነዋል።

Exit mobile version