የሀገር ውስጥ ዜና

ኅብረ-ብሔራዊነታችንን ማጠናከር ይገባል – አቶ አዲሱ አረጋ

By ዮሐንስ ደርበው

September 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረ-ብሔራዊነታችንን በማጠናከር የተጀመሩ ሁለንተናዊ ስኬቶችን ማስቀጠል ይገባል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ አዲሱ አረጋ ገለጹ፡፡

በኦሮሚያ ክልል የኅብር ቀን “ኀብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው፡፡

አቶ አዲሱ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ኅብረ-ብሔራዊነታችንን በማጠናከር የተጀመሩ ሁለንተናዊ ስኬቶችን ማስቀጠል ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ የሚሆኑባትን ሀገር ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

አባቶቻችን በአንድነት ዓድዋ ላይ ድል እንዳደረጉት ሁሉ የአሁኑ ትውልድም ኅብረቱን አጠናክሮ የሁላችንም ተስፋ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ዳር ለማድረስ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡