Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 4 የህብር ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ በመከበር ላይ ይገኛል።

ዕለቱ በአሶሳ ከተማ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና በሌሎች ሁነቶች በመከበር ላይ ነው፡፡

የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ተወካይ አጠይብ ሙሐመድ በዚህ ወቅት÷ ጸጋዎቻችንን ይዘን ለሀገራችን ሰላም እና ዕድገት በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል።

ኅብራችንን ከምንገልጽባቸው ሁነቶች አንዱ ስፖርት ነው ያሉት ተወካዩ፤ በስፖርታዊ እንቅስቃሴው አካላዊና አእምሯዊ ጤናችንን በመጠበቅ በልማቱ መሳተፍ አለብን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version