አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለነገ መልካም ፍሬ ዛሬ የሚዘራ ምርጥ ዘር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰመር ካምፕ 2024 ሰልጣኞች የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ተመራቂ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን አበረታተዋል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠረለትን አላማ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናረዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 200 ከፍ አድርጓል፡፡
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ 3 ሺህ 500 ተማሪዎች ተመዝግበው መስፈርቱን ያሟሉ 200 ተማሪዎች በዘንድሮው ክረምት እንዲሰለጥኑ መደረጉን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ስልጠናው በአምስት ዘርፎች እንደተከናወነ ገልጸው÷ በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ የእውቀት ባለቤት የሆኑ ወጣቶችን ማፍራት ተችሏል ብለዋል፡፡
ስልጠናው በዘርፉ እውቀት ባለቸው አሰልጣኞች ከተሟላ ግብዓት ጋር በመቅረቡ በዘርፍ ብዙ እውቀትና ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ሰልጣኞች ገልጸዋል።
በፍሬሕይወት ሰፊው