የሀገር ውስጥ ዜና

በኅብር ሆነን የትናንት ትግላችንን እና የዛሬ ጥንካሬያችንን ለትውልድ እናስተላልፋለን-ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር፣ኢ/ር)

By amele Demisew

September 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኅብር ሆነን የትናንት ትግላችንን እና የዛሬ ጥንካሬያችንን እየዘከርን ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር፣ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በሌሎች ሁነቶች መከበር ጀምሯል።

በመረሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር፣ኢ/ር) ÷ኅብር ማለት የተለያዩ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሐይማኖት እና የባህል ልዩነቶች ሳይገድበን በኅብር በጋራ የምንቆምበት ነው ብለዋል፡፡

የራሳችንን ማንነት እየጠበቅን አርበኝነትን በመላበስ በኅብር ሆነን የትናንት ትግላችንንና የዛሬ ጥንካሬያችንን በአግባቡ እየዘከረን ለመጭው ትውልድ ማስተላላፍ ይጠበቅብናል ሲሉም መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡