Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የክልሉ መንግሥት እየሠራ መሆኑን ገለጹ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከአቶ ደስታ ጋር የተወያዩ ሲሆን÷ በዚሁ ወቅት የክልሉ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሸ እየሰጠ መሆኑን በመግለጽ ይህን ቁርጠኝነት እንዲያስቀጥል አባላቱ ጠይቀዋል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ፣ ግብርና፣ ሌማት ትሩፋት፣ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የተከናወኑ ተግባራት፣ በንፁህ መጠጥ ውኃና በሰላም ግንባታ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸው ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

በአንጻሩ ከመንገድና ውኃ ጥገና፣ ምርጥ ዘር አቅርቦት፣ መብራትና በይነ-መረብ አኳያ ከሕዝቡ ጥያቄ መኖሩን በማመላከት÷ ቅሬታዎችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን እንደሚሠሩ አስረድተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በበኩላቸው÷ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version