የሀገር ውስጥ ዜና

የ “ኅብር ቀን” “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ ነገ ይከበራል

By Mikias Ayele

September 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ “ኅብር ቀን” አካታች ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ማሳካትና ማጽናት በሚያስችሉ መርሐ-ግብሮች እንደሚከበር የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የሀገረ-መንግሽት ግንባታ ታሪክ ኅብር ኢትዮጵያውያን የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች በጋራ የሚያልፉበት ስውር ስፌት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 በተለያዩ ዘመናት ኢትዮጵያ ያለችበትን መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ እና ጂኦ-ፖለቲካ መሰረት በማድረግ የተሰነዘሩ ጥቃቶችን በተባበረ ክንድ ማክሸፍ መቻሉንም አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንደ ዓድዋ ያሉ ዘመን አይሽሬ ድሎችን በኅብረት የጻፉ ጀግኖች ሀገር መሆኗን መዘከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የኅብር ቀንን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተከፈለውን መስዋዕትነት ለማሰብ፣ ለዘላቂና አካታች ሀገራዊ ግንባታ ጥቅም ላይ ለማዋል ዝግጅት ተጠናቅቋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኅብር የሉዓላዊነት መሰረታችን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው÷ አባቶች ያቆዩዋትን ሀገር የመጠበቅ አደራ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡