አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንድሪያስ እሸቴ (ፕ/ር) የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴደራል ተፈጸመ።
አንድሪያስ እሸቴ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡
በፕሬዚዳንትነት ባገለገሉበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ወዳጆች ዘመዶቻቸውና የሙያ አጋሮቻቸው በተገኙበት የሽኝት ሥነ-ሥርዓት መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ዘመን ጀምሮ ሕገ-መንግሥት በማርቀቅና በማማከር ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን እና በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ማገልገላቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡