የሀገር ውስጥ ዜና

”ተፈጥሮ በምናንከባክበው ልክ መንፈሳችንን እና ጤናችንን ይንከባከባል”-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

By Meseret Demissu

June 25, 2020

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)”ተፈጥሮ በምናንከባክበው ልክ መንፈሳችንን እና ጤናችንን ይንከባከባል” ሲሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ  ገለጹ

ወይዘሮ አዳነች በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት÷ ”ዛሬ ሸገርን የማስዋብ እና እንጦጦ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ የደረሰበትን ደረጃ ሳይ ተደንቄያለው”ብለዋል።

”የዚህ ፕሮጀክት ፍጥነት፣ ውበት፣ ሰላም እና የሚሰጠው ንጹህ አየር በእጀጉ ያስደስታል÷በዚህ ስራ የተሳተፉ ሁሉ ምስጋና እና አድናቆታችን ይገባቸዋል”ም ነው ያሉት ።

እኛም በአቅራቢያችን ያሉትን የተፈጥሮ ሀብቶች እንዳቅማችን ለመንከባከብና ለማሳመር አምነን ቆርጠን ከተነሳን አካባቢያችንን ሁሉ ” ውብ እና ጤናማ ” ነው የምናደርገው ብለዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።