የሀገር ውስጥ ዜና

ሕዳሴ ግድብ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ታሪክ ቀያሪ ፕሮጀክት ነው – አሸብር ባልቻ (ኢ/ር)

By Melaku Gedif

September 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የጎላ አበርክቶ ያለው ታሪክ ቀያሪ ፕሮጀክት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሸብር ባልቻ (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው እንዳሉት÷ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ማረጋገጫና የአንድነታቸው ካስማ ነው።

የግድቡ አራት ተርባይኖች ሃይል በማመንጨት ላይ መሆናቸውን ገልጸው÷ከእነዚህ ተርባይኖች መካከል ሁለቱ ሥራ የጀመሩት በተጠናቀቀው የነሀሴ ወር መሆኑን አስታውሰዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 13ቱም ተርባይኖች ወደ ሥራ ሲገቡ አምስት ሺህ 150 ሜጋ ዋት ሃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ገልጸዋል።

ይህም ኢትዮጵያ ባለፉት 70 ዓመታት ያመነጨችውን ጠቅላላ ሃይል በእጥፍ የሚያሳድግ ታሪክ ቀያሪ ምዕራፍ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም የህዳሴ ግድብ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የጎላ አበርክቶ ያለው ታሪክ ቀያሪ ፕሮጀክት መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ሀይል ከማመንጨት ባለፈ ያመነጨውን ወደ ተጠቃሚዎች የማድረስ ሀላፊነቱን በትጋት እየፈጸመ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ይህንን ደግሞ ከህዳሴ ግድብ ባለፈ በኮይሻ፣ በጊቤ ሶስትና ሌሎች ማመንጫዎች በጥራትና በፍጥነት በማድረግ አረጋግጧል ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ሃይል ለውጭ ገበያ በማቅረብ የው