Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ መሠራት አለበት- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ለትምህርት ዘርፍ ትኩረት በመሥጠት የክልሉ ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ በትጋት እንዲሠራ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡

21ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባዔ “የማኅበረሰብ ተሳትፎ ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ሐሳብ በሠመራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ሚኒስትሩ በጉባዔው ላይ እንዳሉት÷ ክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ሚኒስቴሩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ለዘርፉ ትኩረት በመሥጠት የክልሉ ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አሚና ሴኮ በበኩላቸው÷ የሴክተሩን ጥራት አስጠብቆ ለማስቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቀናጅቶ መሥራት ከተቻለ ማኅበረሰቡ የሚፈልገውን ጥራት ያለው ትምህርት ማምጣት እንደሚቻል ያመላከቱት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዱ ሐሰን ናቸው፡፡

Exit mobile version