አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ጳጉሜ 3-የሉዓላዊነት ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
ዕለቱን “ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት”በሚል መሪ ሃሳብ ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በኑር ፕላዛ የሰንደቅ ዓላማ ሥነ-ስርዓት በማከናወን ያስጀመሩት።
ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ የከተማ እንቅስቃሴዎችን በመግታት በክልሉ ብዙሃን መገናኛ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ብሔራዊ መዝሙር በማሰማትና በሌሎች መርሐ ግብሮች እንደሚከበርም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።