አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።
“የምስራቁ ጮራ የኢትዮጵያ ወታደሮች ነን” በሚል መሪ ሃሳብ የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት ምስረታ የማጠቃለያ ክብረ በዓል በሐረር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።
የሰራዊት አባላቱ ድጋፉን ያደረጉት ዛሬ የዕዙ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም በተከበረበት ወቅት ነው።
ድጋፉ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች እንደሚውል ተገልጿል።
ድጋፉን ያስረከቡት ኮሎኔል ፈይሳ አየለ÷ ሠራዊቱ ከራስ በፊት ለሀገርና ለህዝብ የሚለውን መርህ በማንገብ የእዙ ሁሉም አባላት የገንዘብ ድጋፉን ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
በተሾመ ኃይሉ