የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገር የምትሻገረው ከትንሽ ተነስተው ወደ ትልቅ ኩባንያዎች በሚያድጉ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

September 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር የምትሻገረው ከትንሽ ተነስተው ወደ ትልቅ ኩባንያዎች በሚያድጉ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ወጣቶች በሰመር ካምፕ የሰሯቸውን የፈጠራ ቴክኖሎጂዎችን ዛሬ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የወጣቶቹ የፈጠራ ስራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።