Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በመጪው ሰኞ ይፋ ይሆናል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት በመጪው ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመላ ሀገሪቱ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 97 ነጥብ 5 በመቶ ወይም 684 ሺህ 205 ያህሉ ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል።

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 29 ሺህ 718 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ ናቸው።

Exit mobile version