አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 144 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ ጎዴቶ÷ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በህግ የተደነገገውን የይቅርታ መሥፈርት የሚያሟሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከይቅርታ ተጠቃሚዎች ውስጥ 43 የህግ ታራሚዎች ሴቶች ሲሆኑ ከእነሱ ጋር በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ 7 ህፃናትም የይቅርታው ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አንድ የህግ ታራሚ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በማምጣቱ በልዩ ሁኔታ የይቅርታ ተጠቃሚ መሆኑን መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።