የሀገር ውስጥ ዜና

ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን

By Feven Bishaw

September 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)”የመሻገር ጥሪቶች የአዲስ ብርሃን ወረቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ ሲከበርም ኢትዮጵያን ለማሻገር በተደረጉ ጥረቶች የተገኙ ስኬቶች እየታሰቡ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ለማሻገር ትልቅ አቅም የፈጠሩ ስኬቶች በሁሉም ዘርፎች ቢመዘገቡም በግብርና ዘርፍ ላይ የተመዘገቡት ድሎች ለመሻገር ቀን የመሻገር ምልክቶች ናቸው።

ለግብርናው ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ለዘመናት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ማስቀረት መቻሉ በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ከተፈጠሩ የመሻገር ጥሪቶች አንዱ ማሳያ ነው።

በስንዴ ሰብል ዓመታዊ ምርት ከነበረበት 50 ሚሊየን ወደ 230 ሚሊየን ኩንታል የማምረት አቅም ተሸጋግሯል።