Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኬኒያ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ17 ተማሪዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ17 ተማሪዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

አደጋው በማዕከላዊ ኬንያ በሚገኘው የሂል ሳይድ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ላይ ሲሆን በአደጋው ከ17 ተማሪዎች ህልፈት በተጨማሪ 14 ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለፀው፡፡

አደጋውን ለመከላከል የነፍስ አድን ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የእሳት አደጋው ምክንያት ተጣርቶ ጥፋተኛ የሆኑ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

በኬንያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተከታታይ የትምህርት ቤት የእሳት አደጋዎች እየተከሰቱ ሲሆን በፈረንጆቹ ከ2001 ጀምሮ በተከሰቱ አደጋዎችበ ከ70 በላይ ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version