የሀገር ውስጥ ዜና

ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን

By Feven Bishaw

September 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)”የመሻገር ጥሪቶች የአዲስ ብርሃን ወረቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ ሲከበርም ኢትዮጵያን ለማሻገር በተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ስኬቶችና በሂደቱ የገጠሙ ተግዳሮቶች እየታሰቡ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ለማሻገር ትልቅ አቅም የፈጠሩ ስኬቶች በሁሉም ዘርፎች ቢመዘገቡም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የተመዘገቡት ድሎች ለመሻገር ቀን “የመሻገር ምልክቶች” ናቸው።

በኢንዱስትሪ ዘርፍ በተለይም ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት በተከናወኑ ተግባራት 2 ቢሊየን ዶላር የሚገመቱ ተኪ ምርቶችን ማምረት ተችሏል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሀገር ውስጥ ምርት በመተካት 2 ነጥብ 315 ቢሊየን ብር የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለማዳን ታቅዶ 2 ነጥብ 844 ቢሊየን ብር በማዳን ከእቅዱ በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል በርካታ አምራች ፋብሪካዎችም ዳግም ወደ ስራ ገብተዋል።