የሀገር ውስጥ ዜና

ማሰልጠኛ ተቋሙ መርከበኞችን አስመረቀ

By amele Demisew

September 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባህረኞች ማሰልጠኛ ተቋም በዘርፉ ያሰለጠናቸውን መርከበኞች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ ከዚህ ቀደም በጣና ሐይቅ ላይ ልምምድ አድርገው ወደ ዓለም አቀፉ የመርከብ ቢዝነስ የተቀላቀሉ እና ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት በማቅናት በመርከበኝነት እየሰሩ የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ተመራቂ መርከበኞቹ በኢትዮጵያ ካሉ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የምህንድስና ተማሪዎች መሆናቸው ተጠቁሟል ።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ÷የስልጠና ተቋሙ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በማሰልጠን ለዓለም አቀፉ የመርከብ አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን ገልጸው ዘርፉን በመደገፍ እያበረከተ ላለው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል ።

ዘርፉ ለሀገራችን ወጣቶች ትልቅ የስራ ዕድል መሆን የሚችል ቢሆንም በሚገባው ልክ አልተጠቀምንበትም ያሉት ሚኒስትሩ ተመራቂዎች ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት በሚኖራቸው የሥራ ስምሪት ሀገርን የሚያስከብር ተግባር እንደሚፈፅሙ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ